Skip to main content

ችግር ፈቺና የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትልን በማጠናከር የገቢ አቅምን የማሳደግና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተመላከተ ።

ህዳር 01/ 2018 (ወልቂጤ)

የማዕኩላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሀ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመቀናጀት እያካሄደ የሚገኘው ድጋፋዊ ክትትል ዛሬም ቀጥሎ በጉራጌ ዞን እና በቀቤና ልዩ ወረዳ የመጠጥ ውኃ ፣ መስኖና ማዕድን ኢነርጂ ዘርችፎ አፈፃፀም ላይ በተለያዩ ሳይቶች የመስክ ምልከታ አካሄዷል ።

በጉራጌ ዞን በተካሄደው ድጋፋዊ ክትትል በእንደጋኝ ወረዳ የቡጫ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ፣ በጉመር ወረዳ የጋዜቦ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ የመስክ ምልከታ ተደርጓል ።

የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶቹ ሕብረተሰቡ ብዙ ርቀት ሳይጓዝ ባለበት አካባቢ ተጠቃሚ እንዲሆን  የተለያዩ ቦኖዎች ተሰርተው ዝግጁ መሆናቸውን የድጋፍ ክትትል ቡድኑ ተመልክቷል ።

በተጨማሪ በጉራጌ ዞን ቸሀ ወረዳ በተለያዩ አካባቢዎች በስራ ላይ የሚገኙ ኳሪሳይቶች እንቅስቃሴ መስክ ምልከታ በማካሄድ በግኝቶች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት የመረጃ ልውውጥ የማካሄድና ግብረ መልስ ተሰጥቷል ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊና የመጠጥ ውኃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሙላቱ ጡሞሮ እንደተናገሩት ምልከታ በተካሄደባቸው የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች ባጠረ ጊዜያት ለህብረተሰቡ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ የማጠናቀቂያ ስራዎችና የፍተሻ ስራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል ።

ችግር ፈቺና የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትልን በሁሉም ዘርፍ በማጠናከር በመስኖ ፣ በማዕድንና በሌሎች ዘርፍ የገቢ አቅምን ለማሳደግ እና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተጠያቂነት መንቀሳቀስ እንደሚገባ ተመላክቷል ።

በቀቤና ልዩ ወረዳ በተካሄደው የመስክ ምልከታ በልዩ ወረዳው የተለያዩ ቀበሌያት /ዘቢሞላ፣ ሌንጫ እና ቆላከባዳ / ለመስኖ ልማት የተገጠሙ ሶላር ፓምፖች   እና  የማዕድን/ካባ ማምረቻ ሳይት ዋነኞቹ ሲሆኑ ምልከታ የተደረገባቸው የመስኖው ልማት ስራዎች በቂ የመሬት ዝግጅት ተደርጎባቻው ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት አርሶ አደሩን ወደ ምርት ለማስገባት የተኬደበት ርቀት አበረታች መሆኑን የክልሉ ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ አቶ ሀይሌ ደዊ ገልፀዋል ።

በመጨረሻም ለመስኖ ልማት የተገጠሙ ሶላር ፓምፖች በሙሉ አቅም ወደ ስራ እንዲገቡ ፣ በማዕድን አለኝታ ጥናትና በመጠጥ ውሀ ዘርፍ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብና የልዩ ወረዳውን ሕዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ ከሚመለከታቸው በመተባበር በልዩ ትኩረት እንዲሰራ የጋራ መግባባት ተፈጥሯል ።

Image