ለሀላባ ቁሊቶ ከተማ የውሃ አገልግሎት ድርጅት የ4.2 ሚሊየን ብር የማቴሪያል ድጋፍ ተደረገ ።
cerwater
Mon, 11/24/2025 - 14:36
ህዳር 11/2018 (ወልቂጤ)
የዓለም አቀፉ በጎ አድራጎት ድርጅት People in Need ፕሮጀክት (PIN) ለሀላባ ቁሊቶ ከተማ የውሃ አገልግሎት ድርጅት በ 4.2 ሚሊየን ብር ግምት የተለያዩ የውሃ ማቴሪያሎችን ድጋፍ አድርጓል።
ማቴሪያሎቹን በይፋ የተረከቡት የከተማው የውሃ አገልግሎት ድርጅት ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ሸምሱ አኒቻ ድጋፉ የከተማዋን የውሃ አቅርቦት ለማሳደግ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።
ይህ ከPeople in Need የተደረገልን የ4.2 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የውሃ ማቴሪያል ድጋፍ፣ በአሁኑ ወቅት የነበረብንን የማቴሪያል እጥረት በመቅረፍ የውሃ አገልግሎታችንን ጥራት እና ቀጣይነት በእጅጉ ያሻሽለዋል ብለዋል።
ድጋፉ የከተማችንን ነዋሪዎች የንፁህ ውሃ ተደራሽነት ለማረጋገጥ ከምናደርገው ጥረት አንጻር ትልቅ ድርሻ ያለው መሆኑን ጠቁመው የፕሮጀክት ድርጅቱን አመስግነዋል ።
Image
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 