ለ20ኛው ብሔር ብሔረሰቦች በዓል የሚያግዝና የሆሳዕና ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሀ አቅርቦት የሚያሳድግ ሥራ መከናወኑን የክልሉ ውሀ ቢሮ አስታወቀ ።
ህዳር 16/2018 (ወልቂጤ)
ለ20ኛው ብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች በዓል አከባበር የሚያግዝና የሆሳዕና ከተማ የንፀህ መጠጥ ውሀ አቅርቦት የሚያሳድግ ስራ የክልሉ ውሀ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ በክልሉ መንግስት በተሰጠው ትኩረት መሠረት ከሚመለከታቸው ጋር በመቀናጀት ተፈፃሚ ማድረጉን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ ገልፀዋል ።
በክልሉ መንግስት ልዩ ድጋፍና ትኩረት የጥልቅ ጉድጓድ ቁፋሮ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ውሀ ሥራዎች ድርጅት በማከናወን ከፌደራል ውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር በተደረገ የፓምፕ ድጋፍ ለሆሳዕና ከተማ ተጨማሪ የንፁህ መጠጥ ውሀ የማቅረብ ሥራ በተሳካ መንገድ መከናወኑን የቢሮው ሃላፊ አስታውቀዋል ።
በዚህ ሂደት የፓምፕ ተከላና ገጠማ ሥራ በክልሉ ውሀ ቢሮ የኤሌክትሮ መካኒካል ቡድን በስኬት መጠናቀቁን አቶ ዳዊት ተናግረዋል።
የግፊት መስመር ዝርጋታው በሆሳዕና ውሀ ሥራዎች በማካሄድ ውሀው ወደ ማጠራቀሚያ ገንዳ በተሳካ ሁኔታ እንዲገባ ተደርጓል ብለዋል ።
ስራውን የክልሉ ውሀ ቢሮ፣ የሐዲያ ዞን ውሀ መምሪያ፣ የሆሳዕና ከተማ አስ/ እና የከተማው ውሀ አገልግሎት አመራርና ባለሙያዎች በተቀናጀ መንገድና በከፍተኛ ርብርብ ውጤታማ ማድረግ ተችሏል።
Wolkite , Ethiopia
cerswimb10@gmail.com
+251113658301 