Skip to main content

በላይኛው ብላቴ ተፋሰስ አካባቢ ለሚካሄድ የከርሰ ምድር ሀብት አለኝታ ልየታ ጥናት ጉድጓድ ውኃ ቁፋሮ የሚውል ዘጠኝ ቦታዎች/site ርክክብ መካሄዱን ቢሮው አስታወቀ ።

ታህሳስ 09/2018 (ወልቂጤ)

በውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር እየተተገበረ የሚገኘው የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት አካል የሆነው በላይኛው ብላቴ ተፋሰስ አካባቢ ለሚያካሄደው የከርሰ ምድር ውሃ ሀብት አለኝታ ልየታ ጥናት ጉድጓድ ቁፋሮ የሚውል በክልሉ በሚገኙ አራት ዞኖች ውስጥ ዘጠኝ ቦታዎች / site ለአሸናፊ ተቋራጮችም ማስረከብ መቻሉን በቢሮ ኅላፊ ማዕረግ የክልሉ ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ምክትልና የውሀ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ አለይካ ሽኩር ገልፀዋል ።

በዛሬው ዕለት በከምባታ ዞን በአንገጫ እና አዴሎ ወረዳዎች ሀለት ቦታዎችን/Site ሀይድሮ ኢንጂነሪንግ ድርጅት እንዲረከብ መደረጉን ተናግረዋል ።

የቁፋሮው አላማው ከአገልግሎቱ ባሻገር የከርሰ ምድር ውሃ አለኝታ /potential በአቅም በጥረት ማወቅና ለቀጣይ ጥናት በተደረጉ አካባቢዎች ላይ የውሀ ጉድጓድ ቁፋሮ ቦታዎችን ዲዛይን ለማድረግ መሆኑን ወ/ሮ አለይካ ገልፀዋል ።

በቦታ ርክክቡ ላይ የተገኙት የከምባታ ዞን ውሀ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ምክትል ሃላፊ አቶ አብነት ወትሮ በበኩላቸው የቁፋሮ ስራው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ እንዲሁም የውሀ ግኝቱን ተከትሎ ለሚከናወኑ ተግባራት መምሪያውም ሆነ የሚመለከታቸው የክልል እና ዝአካላት የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል ።

በርክክቡ ወቅት ከፎደራል ሲኒየር ሀይድሮጂኦሎሲስት አቶ ገለቲ በላይ፣ የክልል ፣ የዞንና የየወረዳዎቹ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል ።

Image