Skip to main content

የመሰረተ ልማት ፕሮጀክት ግንባታዎችን እስከ ጥር/2018 በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ ።

ታህሳስ 14/2018 (ወልቂጤ)

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ  ኃላፊ  ዶ/ር መሀመድ ኑሪዬ በተገኙበት የሁሉ አቀፍ ገጠር ተደራሽ መንገድ፣የገጠር መንገድ፣ የመጠጥ ውሃ እና የመስኖ ፕሮጀክቶችን እስከ ጥር ወር 2018 ተጠናቀው ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ፕሮጀክቶች በመለየት አፈፃፀማቸው የደረሰበትን ማሳያ ሰነድ በዘርፉ ኃላፊዎች ቀርቦ ግምገማ ነክ ውይይት ተካሂዷል ።

በግምገማ ወቅት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሀላፊ  ዶክተር መሀመድ ኑሪዬ እንደገለፁት የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች በዘላቂነት እንዲያገለግሉ ከግንባታቸው ባሻገር የተዘረጉ ስርዓቶችን በደንብ አጠናክሮ መሄድ ያስፈልጋል ብለዋል።

አክለውም  የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን በተቻለን አቅም ተደራሽነታችን እያሰፋን ነባሮችን በማጠናቀቅ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን እናስጀምራለን ብለዋል ።

የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ለማህበረሰብ አገልግሎት ክፍት እንዲሆን ጥብቅ ድጋፍ እና ክትትል እንደሚያስፈልግ በአጽኖት  አሳስበዋል።

በመጨረሻም በክልሉ ባሉት  በዞን እና በልዩ ወረዳ የሚገኙ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት ለማብቃት የታቀዱ ፕሮጀክት አፈጻጸማቸውን ወደ ፕሮጀክቶች በመሄድ የመስክ ምልከታ እንዲታይ ስምሪት ተሰጥቷል።

በመድረኩም የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ፣የውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ ፣የመስኖ  እና መንገዶች ባለስልጣን አመራሮች  ተሳትፈዋል ።

Image