በላይኛው ብላቴ ተፋሰስ አካባቢ ለሚካሄድ የከርሰ ምድር ሀብት አለኝታ ልየታ ጥናት ጉድጓድ ውኃ ቁፋሮ የሚውል ዘጠኝ ቦታዎች/site ርክክብ መካሄዱን ቢሮው አስታወቀ ።

ታህሳስ 09/2018 (ወልቂጤ)

በውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር እየተተገበረ የሚገኘው የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት አካል የሆነው በላይኛው ብላቴ ተፋሰስ አካባቢ ለሚያካሄደው የከርሰ ምድር ውሃ ሀብት አለኝታ ልየታ ጥናት ጉድጓድ ቁፋሮ የሚውል በክልሉ በሚገኙ አራት ዞኖች ውስጥ ዘጠኝ ቦታዎች / site ለአሸናፊ ተቋራጮችም ማስረከብ መቻሉን በቢሮ ኅላፊ ማዕረግ የክልሉ ውሀ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ምክትልና የውሀ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ አለይካ ሽኩር ገልፀዋል ።

በዛሬው ዕለት በከምባታ ዞን በአንገጫ እና አዴሎ ወረዳዎች ሀለት ቦታዎችን/Site ሀይድሮ ኢንጂነሪንግ ድርጅት እንዲረከብ መደረጉን ተናግረዋል ።

የቁፋሮው አላማው ከአገልግሎቱ ባሻገር የከርሰ ምድር ውሃ አለኝታ /potential በአቅም በጥረት ማወቅና ለቀጣይ ጥናት በተደረጉ አካባቢዎች ላይ የውሀ ጉድጓድ ቁፋሮ ቦታዎችን ዲዛይን ለማድረግ መሆኑን ወ/ሮ አለይካ ገልፀዋል ።

በቦታ ርክክቡ ላይ የተገኙት የከምባታ ዞን ውሀ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ምክትል ሃላፊ አቶ አብነት ወትሮ በበኩላቸው የቁፋሮ ስራው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ እንዲሁም የውሀ ግኝቱን ተከትሎ ለሚከናወኑ ተግባራት መምሪያውም ሆነ የሚመለከታቸው የክልል እና ዝአካላት የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል ።

በርክክቡ ወቅት ከፎደራል ሲኒየር ሀይድሮጂኦሎሲስት አቶ ገለቲ በላይ፣ የክልል ፣ የዞንና የየወረዳዎቹ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል ።

Image

የቢሮ ኃላፊ መልዕክት

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ መልዕክት 

            አቶ ዳዊት ሃይሉ ገሮ 

ኢትዮጵያ አገራችን በተለያዩ ወንዞች፣ ጅረቶች፣ ሐይቆች እና የውሀ አካላት የታደለች እና በተፈጥሮ ፀጋ የተቸረች ሀገር ከመሆኗም በላይ በአስራ ሁለት ትላልቅ የውሀ ተፋሰሶች የተከፈለች አገር ናት፡፡ ምንም እንኳን የተለያዩ ወንዞችና ሐይቆች ባለቤት ብንሆንም የውሀ ሀብቶቻችንን እንደ ሀገር ሙሉ በሙሉ በተገቢው መንገድ መጠቀም አለመቻላችን በውስጣችን ቁጭት እንዲፈጠር አድርጓል፡፡ ከዚህ አንፃር  የውሀ ሀብቶቻችንን እና የተፈጥሮ ፀጋዎቻችንን በአግባቡ በማልማት፣ በማበልፀግና ለዜጎቻችን ምቹና ተስማሚ በማድረግ ጥቅም ላይ ለማዋል የውሀ ሀብቶቻችንን የማልማት፣ የማስተዳደር፣ የመንከባከብ እና በተገበው መንገድ ለመገልገል በመንግስት ረገድ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡  

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሰጥ ከላይ ከተገለጹት እንደ አገር ካሉን አስራ ሁለት ተፋሰሶች መካከል ሁለት ትላልቅ የኦሞ ጊቤ እና የስምጥ ሸለቆ ተፋሰሶች በክልላችን በሚገኙ አካባቢዎች  የሚያቋርጡና በርካታ የክልልን ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተፋሰሶች  ናቸው፡፡ እነዚህ ተፋሰሶች በርካታ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢከኖሚያዊ ጥቅሞች ለክልሉ ማህበረሰብ የሚሰጡ ናቸው፡፡ እንደሚታወቀው የግልገል ግቢ ሁለት የውሀ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በኦሞ ጊቤ ተፋሰስ ላይ የተመሰረተና በየም ዞን ውስጥ የሚገኝ የተፋሰሱ ትልቁ ቱሩፋትና ልዩ ትኩረት የሚፈልግ አካባቢ ነው ተጨማሪ ያንብቡ 

የቢሮው አመራሮች

አቶ ዳዊት ሃይሉ ገሮ
የቢሮ ሃላፊ

ወ/ሮ አለይካ ሽኩር ሸውሞላ 
በቢሮ ኃላፊ ማእረግ የውሃ /ሀብ/ጥና/ አስ/ ዘርፍ ሃላፊ እና ም/ቢሮ ሃላፊ

ኢ/ር ካሳዬ ተክሌ ስራ 
የመስኖ ኤጀንሲ ዋና ስራ አስከያጅ

አቶ መኮን መኔዶ ቀልቦሬ 
የማ/ኢነ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር

ኢ/ር አየለ ኬርጋ ድላጋ
የውሃ ሀብ/ጥና/ዲዛ ዘርፍ ሃላፊ እና ም/ቢሮ ሃላፊ

አቶ ሙላቱ ጡሞሮ ራሸ 
የመ/ው/አቅ/ሳን ዘርፍ ሃላፊ እና ም/ቢሮ  ሃላፊ

አቶ ሀይሌ ደዊ ገ/ማርያም
የቢሮ ሃላፊ አማካሪ

ኢ/ር መሀመድስራጅ አ/ቋድር ኢብራሂም  
የመስኖ ኤጀንሲ  ም/ስራ አስኪያጅ

ዜና

በዋን ዋሽ ፕሮግራም ከ115 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን ለማስገንባት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን…
በክልሉ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶች ውጤታማ ናቸው:-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ የሳንኩራ ባለብዙ መንደር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ምርቃት ላይ ያስተላለፉት…
በዩኒሴፍ በጀት ድጋፍ ከ40 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የበሸኖ ስንቢጣ ሶላር ፕሮጀክት ተመረቀ
በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በ1ኛ ጤፎ ቀበሌ ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባ የውሃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት እየተመረቀ…
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር እየተሰራ ያለው ስራ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ነው:- መሀመድ ኑሪዬ (ዶ/ር)
በሀድያ ዞን ጎምቦራ ወረዳ ከ10.8 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት…
የብሔራዊ ዋን ዋሽ ፕሮግራም (One WASH National Programme - OWNP) ባለፉት ስድስት ዓመታት አመርቂ ውጤት…

ሚዲያ

        
See More Videos

      

 

ባለድርሻ አካላት

 
  Image 3Image 3Image 4Image 5      Image 6

ስለ ቢሮው አስተያየት መስጫ